አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዋሽ ባንክ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የገቢ አቅምን ለማጎልበት የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የአዋሽ ባንክ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይርጋ ይገዙ ÷ የክልሉን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ድጋፉ ማድረጉን ተናግረዋል።
አዋሽ ባንክ በቀጣይም ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ ÷ ባንኩ ያደረገው ድጋፍ ትርጉም ያለው መሆኑን ጠቅሰው፥ አዋሽ ባንክ ለክልሉ ድጋፍ ማድረጉ የሚያስመሰግነው ነው ብለዋል።
በወርቃአፈራው ያለው