የሀገር ውስጥ ዜና

“ስለ ኢትዮጵያ” የፓናል ውይይት በደሴ ከተማ ተካሄደ

By Shambel Mihret

August 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ስምንተኛው “ስለ ኢትዮጵያ” የፓናል ውይይት “የጋራ እሴቶቻችን ስለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሃሳብ በደሴ ከተማ ተካሂዷል።

በስምንተኛው ስለ ኢትዮጵያ የፓናል ውይይት ላይ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እና ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በዚሁ ወቅት÷ “ደፋር ጥያቄ መጠየቅ ካልቻልን ደፋር መልሥ ማግኘት አንችልም” ሲሉ ተናግረዋል።

“የምንነጋገረው ስለኢትዮጵያ ነውና ወጣቱ አንድ አይነት መዝሙር እየዘመረ ነው ወይ? ብለን መጠየቅ አለብን፤ ወጣቱ ምን እያለ ነው? ሴቶች እናቶች ምን እያሉ ነው? ብለን መጠየቅ አለብን” ብለዋል።

እንደ አገር የሚታዩ ችግሮችን ለመንግሥትና ለሌላው እየሰጠን የምንሄደው ነገር መፍትሄ አያመጣም ያሉት ዑስታዝ አቡበከር ደግሞ÷ ችግሩ የጋራ ነውና በጋር እንስራ ብለዋል።

በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የፕሬዚዳንቱ የህዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት አማካሪ አቶ ግርማ የሺጥላ በበኩላቸው÷ ከማንም በላይ ለነጻነት ዋጋ የከፈልንና ያሸነፍን ህዝብና አገር ነን፣ እርሥ በርሣችን የምንጠፋፋ ከሆነ ነጻነቱን ለምን እንፈልገዋለን? ለምንስ ዋጋ ከፈልን” ሲሉ ጠይቀዋል።

ሠከን ብሎ መወያየት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው÷ ከሠብዓዊ ባህሪያችን የተነሳ ወደ ጥፋት የሚያመሩንን ነገሮች መተው አለብን፣ ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ቦታ ላይ ሆነን ስንነጋገር በጋራ እሴት በጋራ ሆነን አገር መገንባት አለብን ሲሉም ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች እንግዶች መታደማቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!