አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በአፍሪካ የሚያደርጉትን ጉብኝት ደቡብ አፍሪካ በመግባት ጀምረዋል፡፡
ጉብኝቱ አንቶኒ ብሊንከን ሩሲያ በአፍሪካ ያላትን ተፅዕኖ ለማሳደግ የምታደርገውን ጥረት ለመመከት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በዚህም የመጀመሪያ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ደቡብ አፍሪካ በመግባት ጀምረዋል፡፡
ባለፈው ወር የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት የአፍሪካ ሀገራትን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡
ከፕሪቶሪያ በኋላ ብሊንከን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሩዋንዳን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!