አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 5 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ተደረገ።
የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሃጎስ ጎደፋይ በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ያሉ መረጃዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ሆኗል።
በዚህ መሰረት ህብረተሰቡ 6244 ነጻ የስልክ መስመርን ከዛሬ ጀምሮ በመጠቀም ቫይረሱን በሚመለከት መረጃዎችን ማድረስ ይችላል ብለዋል።
በክልሉ ቫይረሱን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ሃላፊው አስታውቀዋል።