የሀገር ውስጥ ዜና

ብልፅግና ፓርቲ ሀገሪቱ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Tibebu Kebede

March 14, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብልፅግና ፓርቲ በመላው ሀገሪቱ ካደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ካገኘው ሀብት ውስጥ 100 ሚሊየን ብር ሀገሪቱ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት አበረከተ።

በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደው የምስጋና እና የገቢ መሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዐቢይ አህመድ ገንዘቡ የጤና ሚኒስቴር ቫይረሱን ለመከላከል የንፅህና መጠበቂያን ለማሟላት ለሚያደርገው ጥረት የሚውል መሆኑን አስታውቀዋል።

ከዚሁ ጋር አያይዘው ቫይረሱ ጥንቃቄ የሚሻ፤ በመርበድበድ ሳይሆን ንኪኪ እየቀነስን የምንከላከለው ነው ብለዋል።

በዚህ ቫይረስ አንድም ኢትዮጵያዊ ህይወቱ እንዳያልፍ መንግስት እንደሚሰራም ነው ያረጋገጡት።