አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቋም መለኪያ ጨዋታ ከኡጋንዳ አቻው ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የኡጋንዳ አቻውን 1 ለ 0 አሽንፏል፡፡
የብሄራዊ ቡድኑን የአሸናፊነት ጎል የፋሲል ከነማው የመሐል ተጫዋች በዛብህ መለዮ 93ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በቀጣይ እሁድ ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታቸውን እንደሚያከናውኑ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ ቀድም ሲል በአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮንሺፕ /ቻን/ ውድድር ደቡብ ሱዳንን ያሸነፈ ሲሆን ከሩዋንዳ ለሚጠብቀው የደርሶ መልስ ጨዋታ ዝግጅት ሲደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡