የሀገር ውስጥ ዜና

ከ700 ሚሊየን ብር በላይ የተገነባው የመኪና መገጣጠሚያ ተመረቀ

By Mikias Ayele

August 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ700 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተመርቆ ስራ ጀመረ።

ፋብሪካው፥ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በኤል አውቶ ኢንጂነሪንግ እና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ ማህበር ነው የተገነባው።

በምረቃ ሥነስርዓቱ  ላይ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ሳንዱካን ደበበ፥ “ሀገራችንን ወደ ብልጽግና ለማሸጋገር በሚደረገው ጉዞ ወስጥ ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች በሌሎቹ የሀገሪቱ አከባቢዎችም  ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይግባል” ብለዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በበኩላቸው፥  መሰል ስራዎችን በቀጣይ ለሚያከናውኑ ባለሀብቶች የከተማ መስተዳድሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት በቀን 20 መኪናዎችን እየገጣጠመ ለገበያ እንደሚያቀርብ ተመላክቷል፡፡

በነስሪ ዩሱፍ