አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የአሸንድዬ በዓልን ለማክበር ላሊበላ ከተማ ገብተዋል፡፡
እንዲሁም የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለና ሚኒስትሮች በዓሉን ለማክበር ላሊበላ ከተማ መግባታቸውን ከላሊበላ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናቱ ላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታብልና የላሊበላ ከተማ አስተዳደርና የላስታ ወረዳ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።