ስፓርት

በብራዚል እና አርጀንቲና የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

By Mikias Ayele

August 22, 2022

በብራዚል እና አርጀንቲና በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ እና በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄዱ የግማሽ ማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር አሰፋ በቀለ በ1 ሠዓት ከ3 ደቂቃ ከ52 ሠከንድ በመግባት ቀዳሚ በመሆን ሲያሸንፍ በሴቶቹ ደግሞ መስታወት ፍቅሬ 1 ሠዓት ከ13 ደቂቃ ከ4 ሠከንድ በመግባት አሸንፋለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ፋንቱ ገላሳ በሴቶች ግማሽ ማራቶን በሦስት ሰኮንድ ዘግይታ 1 ሠዓት ከ13 ደቂቃ ከ7 ሠከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድርም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል።

በወንዶች ግማሽ ማራቶን ገርባ በያታ 1 ሠዓት ከ29 ሠከንድ በመግባት ሲያሸንፍ የሀገሩ ልጅ ድንቅዓለም አየለ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።

በሴቶች ደግሞ አታላይ አንሙት 1 ሠዓት ከ7 ደቂቃ ከ59 ሠከንድ በመግባት ሁለተኛ ስትወጣ ዘውዲቱ አደራው ደግሞ በውድድሩ 5ኛ እንዲሁም ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አዲስዓለም በላይ 9 ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቸውን ከሪዮ እና ቦነስ አይረስ ማራቶን ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡