አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠራዊቱን ወቅታዊ ሁኔታ፣ ባልተረጋገጡ፣ ባልተገቡ መረጃዎችና አሉባልታዎች የመዘገብ ወይም የማራገብ አሉታዊ ሙከራዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የመከላከያ ሚኒስቴር አሳሳበ።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የህዝቡ ድጋፍ እና ተሳትፎ ጠንካራ መሆን፤ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ሉዓላዊነትን ለመጠበቅ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ወሳኝ መሆኑን በፅናት ያምናል ብሏል፡፡