የሀገር ውስጥ ዜና

የካሜሩን ንግድ ምክር ቤት ልዑካን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩትን ጎበኘ

By Feven Bishaw

August 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የካሜሩን ንግድ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩትን የስራ እንቅስቃሴና የስልጠና አካዳሚ ጎብኝቷል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት በቀለና ሌሎች የስራ ክፍል ሀላፊዎች ለልዑካን ቡድኑ የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡