አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በብራዚል መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ሉዊዝ ኤዱአርዶ ዴ አጊአር ቪላሪንሆ ፔድሮሶ ላደረጉት አስተዋጽኦ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አመሰገኑ፡፡
ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የብራዚል አምባሳደር ሉዊዝ ፔድሮሶን አሰናብተዋል።
በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ እና ብራዚል ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግና እንዲጠናከር አምባሳደሩ ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አምባሳደር ሉዊዝ ፔድሮሶ በበኩላቸው÷ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ዜጎቻቸውን ከበርካታ አገራት ለማውጣትና የኮቪድ-19 የመከላከያ ቁሶችን በማመላለስ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሰጠው አገልግሎት አመስግነዋል፡፡
በሌላ በኩል ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አዲስ የተሾሙትን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሴቶች ጉዳይ ድርጅት በአፍሪካ ህብረትና በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ልዩ ተወካይ አዋ ንዳይ ሴክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም÷በአፍሪካ የሴቶችን መሪነትና ተሳትፎ በተመለከተ መደረግ ስላለባቸው ጉዳዮች መክረዋል፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!