ስፓርት

ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

August 24, 2022

አዲ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር ላለበት የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ፡፡

ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር ለሚኖራት የደርሶ መልስ ጨዋታ ዝግጅት ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ የተላለፈ ሲሆን÷ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ተደርጓል።