የሀገር ውስጥ ዜና

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የልማት ሥራዎችን ጎበኘ

By ዮሐንስ ደርበው

August 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የአመራሮች ልዑካን ቡድን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኘ፡፡

ልዑኩ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በአሶሳ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ተመልክቷል፡፡