አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት የተመረጡ የጁንታውን ወታደራዊ አቅሞች እንደሚመታ አስታወቀ፡፡
መንግሥት እስካሁን ድረስ ለሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቢጠባበቅም ጁንታው ጥቃቱን እንደቀጠለበት አስታውቋል፡፡
በመሆኑም የፌደራል መንግስት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር የገለጸው ዝግጁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፥ ለጁንታው ፀረ ሰላም እብሪት ምንጭ የሆኑ ወታደራዊ አቅሞችን ኢላማ ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ያስታወቀው፡፡
ስለሆነም በትግራይ የሚኖሩ ወገኖች በተለይም የጁንታው ወታደራዊ መሳሪያዎች እና ማሰልጠኛዎች ካሉባቸው አካባቢዎች ራሳችሁን እንድታርቁ ሲል መንግሥት መክሯል፡፡