አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሰላምና ደኅንነት ስለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሐሳብ 10ኛው ስለኢትዮጵያ የምክክር መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በመድረኩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ የውይይቱን ወቅታዊ እና አስፈላጊነት አብራርተዋል፡፡
አክለውም ኢትዮጵያ በዘመናት ሂደት ውስጥ ፈተናዎችን እያለፈች የተሻገረች ሀገር ናት ብለዋል፡፡
የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም “የሰላም ግንባታ ስኬቶች እና ፈተናዎቻቸው” በሚል ርዕስ የመነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል።
ለውጥን የመቃወም ፍላጎት ያላቸው ኃይሎች የኢትዮጵያን ሰላም ማናጋታቸው እና በህወሓት መሪነት ዜጎችን ፈተና ውስጥ በማስገባት የሰላም ችግር በሀገሪቱ መፈጠሩ በቀረበው ጽሑፍ ተገልጿል፡፡
ባለፉት ጊዜያት አንዳንድ የውጭ ኃይሎች፥ የሚዲያ፣ የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ እና የውስጥ ተላላኪዎችን በመመልመል የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ በዘመቻ ጭምር የተደገፈ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውም ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ ፈተናዎች ቢኖሩባትም ሰላምን ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ በውስጥም በውጭም ስለመከተሏ ተገልጿል፡፡
ከመድረኩ መጀመር በፊት የሀገሪቱን የፖለቲካ ታሪካዊ ሂደት የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ ተከፍቷል፡፡
በክብረወሰን ኑሩ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!