የሀገር ውስጥ ዜና

ኤጀንሲው ከመስከረም ጀምሮ የቀለም ማኅተም በደረቅ ማኅተም እንደሚቀይር አስታወቀ

By Alemayehu Geremew

August 27, 2022

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ከመጪው መስከረም ወር ጀምሮ የጽህፈት ቤቶቹን የቀለም ማኅተሞች በደረቅ ማኅተሞች እንደሚቀይር አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ታከለ ነጫ ÷ ማኅተሞቹ የሚቀየሩት በከተማዋ የሚስተዋለውን የሰነድ ማጭበርበር ለማስቀረት ነው ብለዋል፡፡

ይህን ተግባራዊ ለማድረግም ኤጀንሲው የብረት ማኅተሞች ከውጭ ማስገባቱን ተናግረዋል፡፡

የአማራና ኦሮሚያ ክልል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎት ተቋም አመራሮችና ባለሙያዎች በኤጀንሲው ተገኝተው የልምድ ልውውጥ ማድረጋቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡