የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የ60/90 ቀናት ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ

By Amele Demsew

August 28, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ከ818 ሚሊየን ብር ወጭ የተደረገባቸው የ60/90 ቀናት ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ።

ከተሰሩ የሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች መካከል የከተማ ግብርና፣ የአረጋውያን የምገባ ማዕከላት፣ የሽገር ዳቦ መሸጫ ማዕከሎች እና መሰል ፕሮጀክቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃ ሰነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፥ ፕሮጀክቶቹ የክፍለ ከተማውን ህዝብ የልማት ፍላጎት የሚመልሱ ናቸው።

በምረቃ ስነስርዓቱ የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡