የሀገር ውስጥ ዜና

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከደቡብ ኮሪያ ውኃ ኮፖሬሽን ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ

By ዮሐንስ ደርበው

August 29, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከደቡብ ኮሪያ ውኃ ኮርፖሬሽን ጋር የትብብር ስምምነት በደቡብ ኮሪያ፣ ሲዎል ተፈራርሟል።

የደቡብ ኮሪያ ውኃ ኮርፖሬሽን ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፓርክ ጄይ ስምምነቱን ከተፈራረሙ በኋላ ባደረጉት ትግግር ÷ የኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ግንኙነት እንደማንኛውም ሀገር የዲፕሎማሲና የልማት ትብብር ብቻ ሳይሆን በደም የታተመ መሆኑን አንስተው ኮርፖሬሽኑ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በአጋርነት ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።