የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ክልል ካቢኔ በጀጎል ግንብ ላይ የሚፈጸሙ ሕገ ወጥ ተግበራትን ለመቆጣጠር ወሰነ

By Feven Bishaw

August 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀጎል ግንብ ውስጥና ዙሪያ የሚስተዋለውን ሕገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ ላይ የቁጥጥርና የክትትል ሥራዎች እንዲጠናከሩ የሐረሪ ክልል ካቢኔ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የክልሉ ካቢኔ የጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ የተቀናጀ ጥበቃና እንክብካቤ ለማድረግ እና የሐረር ከተማ ማዘጋጃቤታዊ ገቢን ለማሳደግ በቀረቡለት ሰነዶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡