የሀገር ውስጥ ዜና

ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሎግያ ሆስፒታል የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ድጋፍ ተደረገ

By Feven Bishaw

August 31, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግሎባል ኤይድ ኢትዮጵያ ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሎግያ ሆስፒታል ግማሽ ሚልየን ዶላር የሚገመት ዘመናዊ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ድጋፍ አደረገ።

የግሎባል ኤይድ ኢትዮጵያ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መላኩ ሥዩም ድጋፉን ለሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መሐመድ ዑስማን አስረክበዋል።