አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽኅፈት ቤት አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዱ።
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እንዳሉት፥ አሸባሪው ህወሓት በተደጋጋሚ ጊዜ የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ወደ ጎን በመተው ለሦስተኛ ጊዜ በሀገራችን ላይ ጦርነት ከፍቷል።
አሻባሪው ህወሓት ለሠላም የተዘረጋውን የኢትዮጵያ እጅ ነክሶ የጀመረውን የጥፋት ጉዞ ለሠላማችን ዘብ በመቆም እንገታዋለን ማለታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውንም መግለጻቸው ነው የተመለከተው፡፡