የሀገር ውስጥ ዜና

የአንበሳ እና ሸገር አውቶብስ አገልግሎት ድርጅቶች ለተሳፋሪዎች የእጅ ማጽጃ ያቀርባሉ – ኢ/ር ታከለ

By Tibebu Kebede

March 16, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንበሳ እና ሸገር አውቶብስ አገልግሎት ድርጅቶች የተሳፋሪዎችን ንጽህና ለመጠበቅ ከዛሬ ጀምሮ የእጅ ማጽጃ አልኮል እንደሚያቀርቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለፁ።

አሽከርካሪዎቹ የእጅ ጓንት የሚጠቀሙ ሲሆን ተሳፋሪዎችም ወደ አውቶቡሶች ሲገቡ ድርጅቱ የሚያቀርበውን የእጅ ማጽጃ አልኮል እጃቸው ላይ አድርገው እንዲገቡ በፌስቡክ ገፃቸው አሳስበዋል።