የሀገር ውስጥ ዜና

ዳያስፖራው ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ የሚያደርግባቸው የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ይፋ ሆኑ

By Shambel Mihret

September 01, 2022

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  የገንዘብ ሚኒስቴር በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመከላከያ ሠራዊትን ድጋፍ የሚያደርጉባቸው የባንክ ሒሳብ ቁጥሮችን ይፋ አደረገ፡፡

ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ÷ የኢትዮጵያ ጠላቶች በሀገራችን  እና በሰላም ወዳዱ ወገናችን ላይ ዳግም ጥቃት በማወጅ የተጠናወታቸውን ኢትዮጵያን የማዋረድ እኩይ ተግባር እንደገና መጀመራቸውን አንስቷል፡፡

ይህንን የተቃጣብንን የተቀናጀ  ጥፋትም ጀግኖቹ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይሎች ከሰላም ወዳዱ ደጀን ህዝባችን ጋር በመሆን በጽናት እና በጀግንነት እየመከቱ ይገኛሉ ነው ያለው።

ይህ ተጋድሎ የሚደረገውም  ለሀገራችን የሚሰነብት፣ የሚከርም፣ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ ሊኖር የሚችል ዘላቂ ሰላም ለማስገኘት  ነው ሲልም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

በውጭ የሚትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም  እንደተለመደው ለዚህ ትግል እያደረጉት ያለውን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚያደርጉባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረትም ፡-

ለዩሮ – 1000439142832 ፣ ለዶላር – 1000439142786 እና ለፓውንድ – 1000443606304 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥሮች የተዘጋጁ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡