የሀገር ውስጥ ዜና

ግድያን ጨምሮ በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሰው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ

By ዮሐንስ ደርበው

September 02, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በከባድ የሰው ግድያ፣ የግለሰቦችን ቤት በማቃጠል እንዲሁም ሕገወጥ የጦር መሣሪያን በመጠቀም ወንጀል የተከሰሰው ካሳሁን ተካልኝ የተባለው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡

በሸካ ዞን ፍትሕ መምሪያ የቴፒ ምድብ ጽሕፈት ቤት ዐቃቤ ሕግ እንድሪስ እሸቱ እንደገለጹት÷ ተከሳሹ በሸካ ዞን በየኪ ወረዳና ቴፒ ከተማ ባለፉት ዓመታት ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ መደፍረስ እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የተለያዩ ወንጀሎችን ፈጽሟል፡፡