የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያን ወርቅ ሲሰርቁ የነበሩ የውጪ ዜጎች ተያዙ

By Meseret Awoke

September 02, 2022

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ወርቅ ሲሰርቁ የነበሩ የውጪ ዜጎች መያዛቸውን ማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ ።

የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሰጡት መግለጫ ለሁለት ሳምንት በተደረገ ዘመቻ ወንጀለኞቹ መያዛቸውን ተናግረዋል ።

በኦሮሚያ ፣ ቤኒሻንጉል እና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች በህገ ወጥ መንገድ ወርቅ ሲያወጡና ሲያዘዋውሩ የተገኙ ተጠርጣሪዎችን ተይዘው እየተጣራ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት። ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር በመተባበር ህገ ወጥ ድርጊቱ ላይ የተሳተፉት በብዛት ቻይናውያን መሆናቸውም ተገልጿል።

ያለጥፋታቸው የታሰሩ ካሉም ተጣርቶ እንደሚለቀቁ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!