የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከእንግሊዝ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

September 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ጵጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሪታንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከእንግሊዝ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም አምባሳደር ተፈሪ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ፥ አሸባሪው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ውድቅ ማድረጉንና በአማራና አፋር ክልሎች ዳግም ወረራ መፈጸሙን አብራርተውላቸዋል፡፡

በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ለሚደረገው የሰላም ውይይት መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው ፥ ብሪታንያ በዚህ ላይ ያላትን አቋም አድንቀዋል።

አክለውም ሚኒስትሯ አሸባሪው ቡድን በአማራ ክልል እያደረገ ያለውን ጦርነት በአስቸኳይ እንዲያቆም ላስተላለፉት መልዕክት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትሯ በበኩላቸው ፥ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎችና አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅና እሱን ተከትሎ እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ ፍላጎት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!