አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉራዋ ወረዳ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፖሊስ አስታወቀ፡፡
አደጋው የደረሰው ትናንት ምሽት 3፡30 አካባቢ ከሀረማያ ወረዳ ተሳፋሪዎችን እና ዕቃ ጭኖ ወደ ጉራዋ ወረዳ ሲጓዝ የነበረ “አይሱዙ” የጭነት ተሽከርካሪ መኪና ልዩ ስሙ ጋምቤላ በሚባል አካባቢ በመገልበጡ የደረሰ ነው፡፡
በአደጋውም የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአምስት ሰዎች ላይ ከባድ በአምስት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር ረዳት ኢንስፔክተር ሽታ ተሰማ ተናግረዋል፡፡
የአደጋው መንስዔ ከፍጥነት ወሰንበላይ ማሽከርከር መሆኑን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡