አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲሱ አመት ኢትዮጵያውያን የሰነቅነውን ራዕይ እውን ለማድረግ በጠንካራና በአዲስ የስራ ባህል ታግዘን ወደፊት መጓዝ አለብን ሲሉ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ህዝብ ለ2015 አዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል÷ አዲሱ አመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር የመከባበርና የመተሳሰብ ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡