የሀገር ውስጥ ዜና

አዳማ ከተማ አስተዳደር 257 የቁጠባ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች አስረከበ

By Mikias Ayele

September 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዳማ ከተማ አስተዳደር የበጎነት ቀንን ምክንያት በማድረግ በ107 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ 257 የቁጠባ ቤቶችን በዛሬው ዕለት ለአቅመ ደካሞች አስረከበ።

የቤቶቹን ቁልፍ ያስረከቡት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ እንደገለፁት፥ የአቅመ ደካሞችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ  ከተማ አስተዳደሩ እየሰራ ነው።

በከተማዋ ባለሀብቶችና በመስተዳድሩ ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ስራዎች መሰራታቸውን አስታውሰዋል።

ቤቶቹ ለአቅመ ደካሞች፣ ለአገር ሉዓላዊነት እየተዋደቁ ለሚገኙ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና የፀጥታ አካላት መተላለፋቸው ጠቅሰዋል።

በቀጣዩ ዓመት ለአቅመ ደካሞች 500 የቁጠባ ቤቶችን ለመገንባት ማቀዱን የጠቀሱት ከንቲባው፥ በጎነት ለራስ በመሆኑ ተጋግዘንና ተደጋግፈን ችግሮቹን ማለፍ አለብን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡