የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ሕዝብ ስም የሚገባው ሰብዓዊ ድጋፍ ለአሸባሪው ቡድን ውሏል – ምርኮኞች

By Meseret Awoke

September 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለትግራይ ሕዝብ ተብሎ የሚገባው የዕርዳታ እህልና መድሃኒት ለአሸባሪው ህወሓት እየዋለ መሆኑን የቡድኑ ታጣቂዎች አጋለጡ፡፡

በወልቃይት ግንባር እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊቱ የሰጡ የቡድኑ ታጣቂዎች እንደገለጹት፥ ንፁሃንን በግፍ መግደል ፣ ንብረት መዝረፍ ፣ መሰረተ ልማቶችን ማውደም የአሸባሪ ቡድኑ አሳፋሪና እኩይ ተግባራት ናቸው፡፡

የሽብር ቡድኑ በተከዜ ወንዝ ላይ የተገነባውን ድልድይ በከባድ መሳሪያ ደብድቦ ጉዳት አድርሶበታል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

አሸባሪው ህወሓት የመከላከያ ሠራዊቱን ምት የመመከት አቅም ስለሌለው አብዛኞቹ ታጣቂዎቹ በየሜዳው ለአራዊት ሲሳይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!