የሀገር ውስጥ ዜና

ሱዳናዊያን ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለጹ

By Feven Bishaw

March 17, 2020

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሱዳናዊያን ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገለጹ።

በቅርቡ ለግድቡ ግንባታ ገቢ ለማሰባሰብ በፕሬዚዳንት  ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ይፋ ተደርጎ ለተጀመረው መርሃ ግብር  ሱዳናውያን የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ሱዳናውያኑ ኢትዮጵያ ከጎረቤትና ከአካባቢው ሀገራት ጋር በመተባበርና በመደጋገፍ የአባይ ተፋሰስን ከግጭት ቀጠናነት ይልቅ የዕድገት ማዕከል ለማድረግ እያከናወነች ያለውን ተግባር እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

የግድቡ ግንባታ እስከሚጠናቀቅም የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑና ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡