የሀገር ውስጥ ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “የአንድነት ቀን” እና የ”ጓንዷዋ” በዓል እየተከበረ ነው

By Shambel Mihret

September 10, 2022

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “የአንድነት ቀን” እና የ”ጓንዷዋ” በዓል የክልሉ ርዕሰ-መስተዳዶር አቶ አሻድሊ ሀሰን በተገኙበት እየተከበረ ነው፡፡

በክልል “የአንድነት ቀን” ከጉሙዝ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ጓንዷዋ” በዓል ጋር በጥምረት አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተለያዩ መርሐ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል፡፡

የጉሙዝ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ጓንዷዋ በዓል “ጓንዷዋ ለሠላም፣ ለፍቅርና ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል ነው በአሶሳ ከተማ እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ አንድነትን የሚያጎለብቱ መልዕክቶችን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶች እየቀረቡ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡