የሀገር ውስጥ ዜና

የደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ለጥምር ሃይሉ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

By Melaku Gedif

September 10, 2022

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በወሎ ግንባር ለሚገኘው ጥምር ሃይል ስድስት ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ 15 በሬዎች እና 70 በጎችን ሲያበረክት÷ የደሴ ከተማ ደግሞ 29 በሬዎች፣ 157 በጎች እና ሌሎች ምግብ ነክ ድጋፎችን አድርጓል፡፡

ጥምር ሃይሉ ጦርነቱን በድል እስኪያጠናቅቅ ድረስ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በለይኩን ዓለም