የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ፈይሰል አልይ ከኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

September 12, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፈይሰል አሊይ ከሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሱልጣን ቢን ሰዕድ አልምሪኺ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በተለያዩ ዘርፎች በትበብር መስራት በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ መወያየታቸውን ከኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!