የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከአፍዴር ዞን ነዋሪዎች ጋር በልማት እና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

By Shambel Mihret

September 12, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በአፍዴር ዞን ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከጸጥታ አካላት ጋር በልማት እንዲሁም ሰላምና ጸጥታን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በአቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ልዑካን አፍዴር ዞን ሀርጌሌ ወረዳ ገብቷል፡፡

ልዑካን ቡድኑ በዞኑና በወረዳው እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድሩ ከዞኑና ከወረዳው የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከጸጥታ አካላት፣ ከወጣቶች፣ ሴቶችና እናቶች ጋር በልማት እና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የክልሉና የፈዴራል መንግስት በዞኑ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ለማሟላትና የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ በቁርጠኛነት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።