የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ናይሮቢ ገቡ

By Feven Bishaw

September 13, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲሱ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ለመታደም ኬንያ፣ ናይሮቢ ገቡ።

ዊሊያም ሩቶ በቅርቡ በሀገሪቱ በተካሄደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የኬንያ አምስተኛ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወቃል።