የሀገር ውስጥ ዜና

የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ካቢኔ ውሳኔዎችን አሳለፈ

By Feven Bishaw

September 13, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ካቢኔው ከተወያየባቸውና ውሳኔ ካሳለፈባቸው አጀንዳዎች መካከል ክልሉ ያለውን ውሱን ሀብት እና ሰፊ የወጪ ፍላጎት ለማጣጣም የሚያስችል ልዩ የወጪና ቁጠባ መመሪያ ይገኝበታል መባሉን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ-መሰተዳድርና ካቢኔ ጉዳዮች ጽ/ቤትያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡