የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን በንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ ህልፈት በተዘጋጀው የሀዘን መግለጫ ፊርማቸውን አስቀመጡ

By Melaku Gedif

September 14, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ ህልፈት በተዘጋጀው የሀዘን መግለጫ ፊርማቸውን አስቀምጠዋል፡፡

ንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል፡፡

የንግሥት ኤልዛቤጥ ሁለተኛ የቀብር ሥነ ሥርዓት የፊታችን መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም የሚፈጸም መሆኑ ታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!