የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት ለዓለምአቀፍ ባለሐብቶች ከፍተኛ ጥበቃ እንደሚያደርግ ገለጸ

By Alemayehu Geremew

September 15, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ለዓለም አቀፍ ባለሐብቶች በማንኛውም ጊዜ የኢንቨስትመንት ጥበቃ ለማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዓለም አቀፍ ባለሐብቶች ማኅበር አባላት በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተሥፋዬ ይልማ እና የኮሚሽኑ አመራሮች ከማኅበር አባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሐብቶች ያለምንም የፀጥታ ሥጋት ኢንቨስትመንታቸው እንዲሳለጥ ከጎናቸው እንደሚቆሙ ማረጋገጣቸውን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡