አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በክልሉ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምሁራን ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያየ፡፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ ፥ ህዝቡ የሀገርን ክብርና የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እየተፋለመ የሚገኘውን የመከላከያ ሠራዊት የመደገፍ ሀገራዊ ግዴታውን ሊወጣ እንደሚገባ አመላክተዋል።
የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ምሁራንም በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከት ከመንግስት ጎን እንዲቆሙና ለሰራዊቱ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።
አሸባሪው ህወሓት የከፈተውን ጦርነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በተባበረ መንፈስ መግታት እንደሚገባም ገልጸዋል።
አክለውም ፥ የኢኮኖሚ አሻጥር በመፍጠር የኑሮ ውድነት እንዲባባስ በሚያደርጉ ነጋዴዎችና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚፈጥሩ አካላትን በማጋለጥ የውስጥ ሰላምን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎችም ፥ አሸባሪው ህወሓት በንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ዘግናኝ ግፍ በማውገዝ ለመከላከያ ሠራዊት ከገንዘብ ድጋፍ ባሻገር እስከህይወት መስዋዕትነት የሚደርስ ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ጦርነቱ ዘርፈ ብዙ ግንባሮች ያሉት መሆኑን ያብራሩት ተሳታፊዎቹ ፥ በሁሉም ግንባሮች በመሰለፍ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ኢትዮጵያ አሸናፊ እንድትሆን እንሰራለን ማለታቸውንም ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!