የሀገር ውስጥ ዜና

የምሥራቅ ባሌ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ

By Shambel Mihret

September 16, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ ባሌ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው የአይነትና የስንቅ ድጋፍ አድርገዋል።

የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር እየተዋደቁ ላሉት የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ደጀንነታቸውን እንደሚያጠናክሩ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

በዞኑ እስካሁን ሁሉንም ወረዳዎች በማስተባበር 65 የእርድ ሰንጋዎችና ከ1 ሺህ የሚበልጡ ፍየሎች ድጋፍ ማድረጉን የዞኑ አስተዳደር ገልጿል፡፡

በሴቶች አደረጃጀት በኩል የተዘጋጀ 254 ኩንታል የአይነት ስንቅም እየተጓጓዘ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የተዘጋጀው ስንቅ ዳቦ ቆሎ፣ በሶ፣ ድርቆሽ፣ ሩዝ፣ መኮረኒና ፓስታን ያካተተ ሲሆን÷ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

የተከፈተብንን ወረራ ለመመከት ሴትና ወንድ ሳንል ሁላችንም ሀገር ለማዳን በጋራ እንነሳ የሚል መልዕክት ነዋሪዎቹ አስተላልፈዋል።

የምሥራቅ ባሌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ኢስማኤል እንደገለጹት÷ በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እየተደረገ የሚገኘው ድጋፍ እንደቀጠለ ነው፡፡