የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 3 ሺህ 656 የእርድ እንስሳት ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

September 16, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ለሁለተኛ ጊዜ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 3 ሺህ 656 የእርድ እንስሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ክልሉ 1 ሺህ 411 ሰንጋ ፣ 1 ሺህ 85 ፍየል ፣ 1 ሺህ 160 በግ በድምሩ 3 ሺህ 656 የእርድ እንስሳት ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡