አዲስ አበባ ፣ መስከረም 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን በኢትዮጵያ ከመስከረም 13 እስከ 15 ቀን 2015 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ ከተማ ይከበራል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ የሚከበረው የቱሪዝም ቀን “አዲስ እሳቤ ለቱሪዝም” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበርም የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ገልፀዋል።
የቤኒሻንጉል ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ የተለያዩ የቱሪዝም መስህቦችን የያዘ እንደመሆኑ እነዚህን ማጉላት የሚያስችሉ ሁነቶች እንደሚኖሩም ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈም ከቤኒሻንጉል ክልል ውጪ በሌሎች ክልሎችም የዓለም የቱሪዝም ቀን ይከበራል ነው ያሉት።
በሁነቱ ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ንቅናቄ እንደሚጀመርም ተገልጿል።
በሜሮን ሙሉጌታ