የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

September 19, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማትም መርሐ ግብሩ እየተካሄደ ነው፡፡

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተገኙት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ፥ በ2014 በጀት ዓመት የተማሪ ውጤት ከማሻሻል አንፃር ከፍተኛ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

አክለውም “ሀገራችን የትውልዱ ነች ያለዚህ ትውልድ ሀገር ልትቀጥልም ልትኖርም አትችልም” ብለዋል።

ስለሆነም ተማሪው እንደ ተማሪነቱ ሀገር የራሱ እንድትሆን ተማሪዎች ተግተው መማርና መስራት እንዳለባቸው ሃላፊው መናገራቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!