የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጠናዊ የሚኒስትሮች ፎረምን እያስተናገደች ነው

By Feven Bishaw

September 19, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ቀጠናዊ የሚኒስትሮች ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

“ቀጠናዊ የክህሎት እና የወጣቶች ሥራ ስምሪት” ቴክኒካል ቡድን ለማቋቋም በተደረገው ስምምነት መሠረት የአባል ሀገራቱ የቴክኒክ ቡድን ማቋቋሚያ ስብሰባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡