አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መጪዎቹ የመስቀል፣ ደመራና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ለማስቻል ያለመ ውይይት ተካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ውይይቱን ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የፀጥታ መዋቅሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር ነው ያደረገው።
በመድረኩ ለሁለቱም በዓላት በተዘጋጀው የፀጥታ አስተዳደር ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ፥ በዓላቱ በርካታ ሕዝብ የሚሳተፍባቸው የአደባባይ በዓላት እንደመሆናቸው በሰላም እንዲከበሩ በፈጣን የመረጃ ልውውጥ የታገዘ የፀጥታ ጥበቃ ሥራ ይከናወናል ነው ያሉት።
ሃላፊዋ አክለውም ፥ ዝግጅቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ የሃይማኖት ተቋማትና ምዕመናን እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማወያየት በፀጥታ ጥበቃ ሥራው ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እንደተሰጠባቸው ከከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!