የሀገር ውስጥ ዜና

የገበታ ጨውን በፎሊክ አሲድና በአዮዲን የሚያበለፅግ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

By Amele Demsew

September 20, 2022

 

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል ጋር በመሆን የገበታ ጨውን በፎሊክ አሲድ እና አዮዲን የማበልፀግ ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል።

 

ፕሮጀክት በፎሊክ አሲድ እና በአዮዲን የበለፀገ የገበታ ጨው የሙከራ ምርትን ለማምረት እና ተቀባይነቱን ለመፈተሽ የሚያስችል ብሎም የነርቭ ህዋሳት ቱቦ የአፈጣጠር እንከኖችን የሚቀንስ ነው ተብሏል፡፡

 

በመሆኑም ኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የሚመረት ብሎም የፎሊክ አሲድ እና የአዮዲን ንጥረ ምግቦች የተካተቱበትን “ጣምራ የገበታ ጨው” ምርት ፕሮጀክትን ነድፏል።

 

ፕሮጀክቱ በወሊድ እድሜ ክልል የሚገኙ እና ታዳጊ ልጃገረዶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

 

ፕሮጀክቱ ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ልገሳ ከ2014 እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ይተገበራል ተብሏል።

 

በፍቅርተ ከበደ