አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ50 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን የተረከቡት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ÷ የክልሉ መንግስት ድጋፍ በአርዓያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል።
ለሰራዊቱ 5 ቢሊየን ብር ድጋፍ ለመሰብሰብ እየተሰራ መሆኑንም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ድጋፉን ያስረከቡት የደቡብ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ ÷ ክልሉ ከዚህ በፊት በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የተከፈተውን ወረራ ለመመከት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።
የደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ባዩሽ ተስፋዬ በበኩላቸው÷ የክልሉ ህዝብ ከድጋፉ ባለፈ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅና በልማት ግንባር ሰፊ ርብርብ እያደረገ ነው ብለዋል።
ክልሉ በህወሓት የሽብር ቡድን የተከፈተውን የሶስተኛ ዙር ጦርነት ለመመከት እየተዋደቀ ላለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በዓይነት ከ220 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ማድረጉን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡