የሀገር ውስጥ ዜና

በንግድ ሽፋን የጦር መሳሪያ ሲነግድ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ

By Feven Bishaw

September 21, 2022

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በመጠጥ ንግድ ሽፋን የጦር መሳሪያ ሲነግድ የነበረ ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና ተተኳሽ ጥይቶችን ጨምሮ 80 ሺህ ሀሰተኛ ብር ተይዟል ተብሏል፡፡